በባሕር ዳር ዙሪያ እና በወንበርማ ወረዳ ጽንፈኞችን የማጽዳት ውጤታማ ሥራ መሥራቱን የምሥራቅ ዕዝ አስታወቀ።

29
ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ በሰሜን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ጽንፈኞችን ከአካባቢው የማጽዳት ውጤታማ ሥራ መሥራቱን ገልጿል።
ዕዙ እንዳለው በተካሄደው ኦፕሬሽን 48 የጽንፈኛ አባላትን ከጥቅም ውጭ ሲያደርግ 40ዎቹ ደግሞ ቆስለዋል ነው ያለው።
ስምሪቱ በተካሄደበት ሞዕራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ ቁጭ ቀበሌ ላይ ስምንት ጽንፈኞች ከጥቅም ውጭ ሲደረጉ 13ቱ መቁሰላቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል ዕዙ በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ አስም ቀበሌ በነበረው ስምሪትም 23 የጽንፈኛው አባላት ከጥቅም ውጭ ሲኾኑ 19 ቆስለዋል ነው ያለው።
በዚህ አካባቢዎቹን ከጽንፈኞች የማጽዳት ተልዕኮ ላይ የጽንፈኛው መሥራች እና አንቀሳቃሽ እንደኾኑ የሚነገርላቸው ቸኮል ዘመኑ፣ ቸኮል ክንዴ፣ በልስቲ ዘመኑ፣ ዳኛው ጥላሁን እና ግርማው መኮነን ከጥቅም ውጭ መደረጋቸውን ነው እዙ የገለጸው።
በተመሳሳይ የጽንፈኛ ማጽዳት ሥራውን በሰሜን ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ዳና ማርያም ቀበሌ የሠራው በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ 17 ጽንፈኞችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ችሏል።
በዚህ ጽንፈኞችን የማጽዳት ሥራም የፌዴራል ፖሊስ አባል የነበረውን የፈቃዱ ቀለመወርቅን ጨምሮ ለጽንፈኞች ስምሪት በመስጠት የሚንቀሳቀሱት ሚኒሊክ ሙላት፣ አንዷምላክ ማረልኝ፣ በቀለ ጥጋቡ፣ አለልኝ ችሎት፣ የጌትነት ካሣ፣ እሱያውቃል አቤ፣ ጥጋቡ አቢታ እና ጌታሁን ካሣሁን የተባሉ ጽንፈኞች ከጥቅም ውጭ ተደርገዋል።
በእነዚህ ስምሪቶች የክልሉ የጸጥታ ኀይል ከሠራዊቱ ጎን ተሰልፎ ያደረገው ጀግንነት የተሞላበት ተጋድሎ ከፍተኛ እንደነበርም ነው የምሥራቅ ዕዝ ሚዲያ የገለጸው።
ሕዝቡ ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ መረጃ በመስጠት እና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የራሱን ሰላም ለመጠበቅ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል ብሏል።
የምሥራቅ ዕዝ ጽንፈኞችን ከሕዝብ ነጥሎ የገቡበት ገብቶ በማጽዳት ሕግ የማስከበሩን ግዳጅ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዘገበው የምሥራቅ ዕዝ ሚዲያ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ድንጋይ ቢሳሳ መሮ አይበሳውም የአባቱን ታሪክ ልጁ አይረሳውም”
Next articleየመና ጤፍ ዝርያ በአርሶ አደሮች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል።