
ደሴ: ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኮምቦልቻ ከተማ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና ከኢንዱስትሪ ፓርክ ውጭ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ተመልክተዋል።
ኢንዱስትሪዎች በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ተኪ ምርት በማምረት እና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ውጤታማ ሥራ እየሠሩ መኾኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናግረዋል።
ባለሃብቶች ያነሷቸው የኀይል አቅርቦት ችግሮች በቅርቡ መፍትሔ እንደሚያገኙም ገልጸዋል።ሌሎች የፋይናንስ እና መሰል ችግሮችን ለመፍታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሠራ አመላክተዋል።
እንደሀገር አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች መሠራታቸውን እና የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር ተግባራዊ እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች ምቹ ሁኔታ እንዳለው ገልጸዋል።
አዳዲስ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ በማስገባት እና የነባሮቹን የማምረት አቅም በማሳደግ በአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ አበረታች ውጤት መመዝገቡንም ተናገረዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሙሐመድአሚን የሱፍ ከተማዋ ለኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት፣ ለትራንሰፖርት እና ሎጅስቲክ ምቹ ከመኾኗም በላይ ሰላም ወዳድ እና ሊሠራ የሚችል ወጣት ያለባት መኾኑን ጠቁመዋል።
ከ10ሺህ በለይ ለሚኾኑ ዜጎች በኢንዱስትሪዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ያነሱት ከንቲባው አልሚዎችን ለመሳብ በሁሉም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ቀልጣፋ እና በዲጂታል የታገዘ ማድረግ ላይ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
በኮምቦልቻ ከተማ 127 ኢንዱስትሪዎች በሥራ ላይ ናቸው። 110 ኢንዱስትሪዎች በግንባታ ላይ መኾናቸው ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ባለ ዓለምየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!