
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 08/2018(አሚኮ) የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ማኅበር “ለአማራ ክልል ሰላም መስፈን የሰላም እናቶች ሚና” በሚል መሪ መልዕክት ምክክር እያካሄደ ነው።
ምክክሩን የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ማኅበር እና የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ናቸው በትብብር ያዘጋጁት።
በመድረኩ ከሰላም እናቶች በተጨማሪ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እየተሳተፋ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት መቅደስ እስጢፋኖስ ማኅበሩ በ2011 ዓ.ም ከተመሠረተ ጀምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
በሀገራዊ ባሕል እና ወግ መሠረት ስለሰላም ተንበርክኮ በመለመንም በእናትነት ጸጋ አለመግባባቶች ወደ ሰላም እንዲቀየሩ ሲሠሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል። እንደ ሀገር የማያግባቡ ጉዳዮች ቢኖሩም በሰከነ መንፈስ በመነጋገር እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ኢትዮጵያውያን ሰላማቸውን እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርበዋል።
በመደረኩ “ሰላምን ለማጽናት የእናቶች ሚና” በሚል ርዕስ ሰነደ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን