ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በባሌ ዞን በመገንባት ላይ ያለውን የዲንሾ ሎጅ እና የጌሴ የሳርምድርን ጎበኙ።

9

ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በባሌ ዞን በመገንባት ላይ ያለውን የዲንሾ ሎጅ እና የጌሴ የሳርምድርን ጎብኝተዋል።

ከአዲስ አበባ በደቡብ ምሥራቅ 400 ኪሎ ሜትሮች ርቀት በኦሮምያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር ስኩዬር በላይ ስፋት ላይ ይገኛል።

ፓርኩ በኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ ደረጃ ያለውን ተራራ ጨምሮ አስደናቂ የመልክዓ ምድር ገጽታዎችን፣ የዱር እንስሳትን፣ ደኖችን፣ የሳር ምድሮችን እና የተለያዩ የተክል ዓይነቶችን በመያዙ “የተለያየ ዓለም በአንድ ፓርክ” ተብሎ ለመጠራት የበቃ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከተለያዩ የመንግሥት ኀላፊዎች ጋር በመሆን ባሌ ዞን ገብተው በመገንባት ላይ ያለውን የዲንሾ ሎጅ፣ ከባቢውን እና የጌሴ የሳርምድርን መመልከታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ለሌሎች ብሎ መኖር ታላቅ የህሊና እርካታ ምንጭ እና የሰብዓዊነት ጥግ ማሳያ ነው” ሙሉነሽ ደሴ( ዶ.ር)
Next articleተገልጋዮችን ለምሬት የሚዳርጉ ብልሹ አሠራሮችን በበቂ ሁኔታ መፍታት ይገባል።