
ደብረማርቆስ: ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
የሞጣ ከተማ አሥተዳደር ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት
“የአርብ ጠንካራ እጆች የወባ ወረርሽኝን ይገታሉ” በሚል መሪ መልዕክት የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ዘመቻን አስጀምሯል።
በዘመቻው የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች እና የከተማው ነዋሪዎች የተጀመረውን ዘመቻ በግንባር ቀደምትነት በመፈፀም ወባን ለመከላከል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የሞጣ ከተማ አሥተዳደር ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አየለ ገረመው የክረምቱ መውጣትን ተከትሎ በከተማዋ እየታየ ያለውን የበሽታ ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሁሉም ቀበሌዎች እየተሠራ ነው ብለዋል።
እስከ ታኅሣሥ/2018 ዓ.ም መጨረሻ ዘወትር አርብ በከተማው የወባ መራቢያ ቦታዎችን በዘመቻ እና ቤት ለቤት የማጽዳት ሥራ ይሠራል ነው ያሉት።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ኀላፊ የሺዋስ አንዱዓለም ወቅቱ የወባ ስርጭት በስፋት የሚስተዋልበት በመኾኑ በሽታውን አስቀድም ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውን ጠቁመዋል።
ሁሉም ማኅበረሰብ አካባቢውን እና ለወባ መራቢያ ምቹ የኾኑ ቦታዎችን በማጽዳት የወባ በሽታን መከላከል አለበትም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን