“ኢትዮጵያ ራሷን ለኢንቨስትመንት ምቹ እያደረገች ነው” የትራንስፖርት የሎጀስቲክስ ሚኒስቴር

5
አዲስ አበባ: ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፓኪስታን – አፍሪካ የንግድ እና ልማት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
ኤግዚቢሽኑ በፓኪስታን የተሠሩ በሚል በርካታ የሀገሪቱ አምራቾች ከኢትዮጵያ ነጋዴዎች ጋር ትስስር ለመፍጠር ማሳያቸውን ይዘው ተገኝተዋል።
በኤግዚብሽኑ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የገበያ ብዝኀነትን ሊመለከት በሚያስችል መልኩ መከፈቱ ጥሩ ነው ብለዋል።
በርካታ ባለሃብቶችም ትኩረታቸውን እዚህ በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል። 250 ሚሊዮን የፓኪስታን ሕዝብ ለአፍሪካ ጥሩ የገበያ መዳረሻ ነው፤ አፍሪካም እንዲሁ ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ደግሞ ለቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ምቹነትን በመፍጠር ላይ ነች ብለዋል። የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ የስንዴ ልማት ማደግ፣ የሌማት ትሩፋት ፕሮጀክት፣ የነዳጅ ማውጣት መርሐ ግብሩ መጀመሩ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያ ራሷን ምቹ ለማድረጓ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
ፓኪስታን በትራንስፖርት ዘርፉ አፍሪካን ለማዳረስ የምታደርገውን ጉዞ ኢትዮጵያ ትደግፋለች ብለዋል።
የፓኪስታን የንግድ ሚኒስትር ጃም ጃማል ካህን የአፍሪካ የ10 ዓመት መሪ እቅድ ከፓኪስታን ጋር ይስማማል ነው ያሉት።
የአፍሪካ ገበያ እንዲሰፋም ፓኪስታን ታግዛለች ብለዋል። በዚህም ለአፍሪካ ዋና አጋር ኾና ለመቀጠል ፓኪስታን ቃል ትገባለች ነው ያሉት።
ባለፈው ጥቂት ዓመታት ብቻ 8 ቢሊዮን ዶላር ፓኪስታን ወደ አፍሪካ ልካለች ያሉት ሚኒስትሩ የሕክምና እቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያዎች፣ የኢንጅነሪንግ ውጤቶች፣ ግብርና እና መሰል ጉዳዮች ትኩረት አድርገን እንሠራለን ብለዋል።
ፓኪስታን ለአፍሪካ በመድኃኒት ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍም አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
ከጥቀምት 6 እስከ ጥቅምት 8 እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽን ኢትዮጵያውያን እንዲታደሙ ጥሪ ቀርቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleማኅበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም በማጽናት የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ ማገዝ አለበት።
Next articleኅብረተሰቡ የፍትሕ አገልግሎትን እንዲያገኝ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው።