ማኅበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም በማጽናት የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ ማገዝ አለበት።

5
ገንዳ ውኃ: ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የገንዳ ውኃ ከተማ ባሕልና ቱሪዝም እና የዞኑ ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ በጋራ በመኾን የዓለም የቱሪዝምን ቀንን “ቱሪዝም ለዘላቂ ለውጥ” በሚል መሪ መልዕክት በገንዳ ውኃ ከተማ አክብረዋል።
በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ46ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ38 ጊዜ ተከብሯል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ጌታቸው አስበው ዞኑ የበርካታ ተፈጥሮዊ እና ሰው ሠራሽ የቱሪዝም ጸጋና ሃብት ያለው አካባቢ መኾኑን አንስተዋል።
ቱሪዝም ለአንድ ሀገር እድገትና ብልጽግና ትልቅ ቆንጮ መኾኑን ተናግረው ዘርፉን የማነቃቃት እና የማስፋፋት ሥራ መሥራት እንደሚገባ አንስተዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ አስያ ኡመር በዓሉ ሲከበር የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን በማስተዋወቅ እና የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት አካባቢውን ማስተዋወቅ እንደኾነም አብራርተዋል።
በዞኑ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ማለትም እንደ አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ፣ ጎደቤ ጥብቅ ደን እና ጥንታዊ የታሪክ መዳረሻ ሥፍራዎች የሚገኙበት አካባቢ መኾኑን ተናግረዋል።
ይህን ሃብት ለማልማት እና ለመጠቀም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። ቱሪዝም ሰላም የሚፈልግ በመኾኑ ማኅበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም በማጽናት የቱሪዝም ዘርፉን ማነቃቃት እና ጸጋውን መጠበቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ሁሉም አካላት የራሱን ባሕል፣ ወግ፣ ልማድ እና እሴት በመጠበቅ ለትውልድ ማስተላለፍ እና የቱሪዝም ዘርፉን አስተዋዋቂ አምባሳደር መኾን ይገባል ነው ያሉት።
በቀጣይ በዞኑ ያሉ ባሕል እና የአመጋገብ ሥርዓት ለሌሎች አካባቢዎች ለማሳወቅ እና ለማስተማር እንደሚሠራም ወይዘሮ አስያ ገልጸዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች በዞኑ ያሉትን ቅርሶች በመንከባከብ እና በመጠበቅ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን በማልማት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እንደሚሠሩም ተናግረዋል።
ማኅበረሰቡ ሰላምን በማስፈን የአካባቢውን ባሕል እና እሴት በመጠበቅ ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየሳይበር ደኅንነት ኦዲትን ያላለፈ የትኛውም ሲስተም ወደ ሥራ አይገባም።
Next article“ኢትዮጵያ ራሷን ለኢንቨስትመንት ምቹ እያደረገች ነው” የትራንስፖርት የሎጀስቲክስ ሚኒስቴር