ከ280 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተከናውነዋል።

3
እንጅባራ: ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የ2017 የክረምት ወራት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመዝጊያ እና የቀጣይ በጋ ወራት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት በ17 የትኩረት መስኮች ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚኾኑ ዜጎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሳተፉ ቆይተዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት፣ የመንገድ ጥገና፣ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ የከተሞች ጽዳት፣ የትምህርት ቤቶች ዕድሳት እና የትምህርት ቁሳቁሶችን ማሠባሠብም በጎ ፈቃደኛ ዜጎች ሲሳተፉባቸው ከቆዩባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል ናቸው።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ቃለአብ ከሃሊ ለሦሥት ተከታታይ ወራት ሲካሄድ የቆየው የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት የተከናወኑበት መኾኑን ተናግረዋል።
በበጎ ፈቃደኞች በተከናወኑ የልማት ሥራዎች ከ280 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲኾን በመንግሥት ይወጣ የነበረውን ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ማስቀረት ተችሏልም ብለዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርት ቅርንጫፍ ጽሕፍት ቤት ኀላፊ እና የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስትሪንግ ኮሚቴ ሠብሣቢ አለሙ ሰውነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግሥት የልማት ክፍተቶችን ከመሸፈን ባሻገር በማኅበረሰቡ ዘንድ ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጎልበት የጎላ ሚና እንደነበረው ተናግረዋል።
የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተዋረድ ባለው የመንግሥት መዋቅር በልዩ ትኩረት የተፈፀመ ስለመኾኑም አንስተዋል።
ባለፉት የክረምት ወራት የነበሩ መልካም ተሞክሮዎችን በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፋት እንደሚገባም ኀላፊው አስገንዝበዋል።
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎ የነበራቸው ወጣቶችም ገንዘባቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ዕውቀታቸውን በማስተባበር የኅብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ሥራዎችን ማከናወናቸውን ተናግረዋል።
በክረምት የነበራቸውን የበጎ ፈቃድ ተሳትፎ በበጋ ወራት ለማጠናከር ቁርጠኛ መኾናቸውንም ወጣቶቹ ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያም በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ እና በማሥተባበር የተሻለ ተሳትፎ ለነበራቸው ወጣቶች እና ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“የክልሉ መንግሥት ለቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleበጎነት ባሕል ኾኖ መቀጠል ይገባዋል።