
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በሰሜን ሸዋ ዞን ቡልጋ ቀጣና ለሰላም አስከባሪ እና ለፖሊስ አባላት ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቅቋል።
በማጠቃለያ ሥነ ሥርዓቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)ን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት መሪዎች ተገኝተዋል።
በማጠቃለያ ሥነ ሥርዓቱ የክልሉን ሕዝብ ሰላም ለመንሳት ጫካ የገቡ ጽንፈኛ ኀይሎች ወደ ማያንሠራሩበት ሽንፈት ውስጥ ገብተዋል ተብሏል።
ሥልጠና የወሰዱ ሰላም አስከባሪ እና ፖሊስ አባላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመኾን የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በጽንፈኛው ኀይል ላይ የማያዳግም ቁርጠኛ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባቸውም ተመላክቷል።
ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሠልጣኞች የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም ተጠይቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!