
ባሕር ዳር: ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ከዩኒሴፍ እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የሚተገብረውን ”ብቁ ወጣት” የተሰኘ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።
የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መላኩ ፈንታ ፕሮግራሙ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚተገበር እንደኾነ በመክፈቻው ላይ ተናግረዋል።
ፕሮግራሙ በሦስት ዓመት ውስጥ በክልሉ የሚገኙ ከ67 ሺህ በላይ ወጣቶችን፤ በአንድ ዓመት ውስጥ ደግሞ 23 ሺህ ወጣቶችን በአዕምሮ ጤና፣ በትምህርት፣ በክህሎት እና በሥራ ፈጠራ ዙሪያ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!