
አዲስ አበባ: ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከተመሠረተ ጀምሮ በሕንፃ ግንባታ ዘርፍ ትላልቅ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በተያዘው በጀት ዓመትም ከ50 በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ወስዶ ግንባታ እያከናወነ መኾኑን የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ታደሰ ግርማ ተናግረዋል። ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ 20 ወለል ሕንፃ ከአሠሪ ተቋማት ውል ወስዶ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደት በአዲስ አበባ ከተማ በመገኘት ጎብኝዋል።
በጉብኝታቸውም ዘመን ኮንስትራክሽን የመገንባት አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
ኮርፖሬሽኑ በግንባታ ጥራት፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ግንባታን በፍጥነት በማጠናቀቅ እና በቅንጅት በመሥራት እያሳየ ያለው እድገት አበረታች ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ተመሥገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!