
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) በጅቡቲ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኮነው ተሾመዋል።
በጅቡቲ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኾነው የተሾሙት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ(ዶ.ር) ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን በመቀበል ቃለ መሐላ ፈጸመዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለተሿሚ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና ጅቡቲን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ የሥራ መመሪያ ሠጥተዋል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!