ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ አጠናቅቆ ሥራ አስጀመረ።

3

ደብረብርሃን፡ ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመገዘዝ የንግድ እና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን አጠናቅቆ አስመርቋል።

የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ይርዳው ዓለሙ ማቀነባበሪያውን ለመገንባት 44 ሚሊዮን ብር ወጭ እንደተደረገበት ተናግረዋል።

ኢንተርፕራይዙ ለሚያረባቸው ከ200 በላይ የወተት ላሞች የመኖ አቅርቦትን ለመሸፈን እና ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ለሚገኙ አርቢዎች መኖ ለማቅረብ ያለመ መኾኑም ተገልጿል።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስማረ መለሰ (ዶ.ር) ኢንተርፕራይዙ ያስመረቀው የመኖ ማቀነባበሪያ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለዕውቀት ሽግግር እና ለልምድ መቀመሪያ ትልቅ አቅም ይኾናል ብለዋል።

ኢንተርፕራይዙ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የወተት አቅርቦት፣ የካፌ አገልግሎት፣ የእንጨት እና የብረታብረት ሥራ፣ የሰብል ማሻሻል፣ የዲዛይን እና ማማከር ሥራን እንደሚሠራም ተናግረዋል።

ከምርቃቱ ጎን ለጎን በዩኒቨርሲቲው በሦሥት ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለው የመምህራን መኖሪያ ሕንጻ ግንባታም ተጎብኝቷል። ግንባታውም 20 በመቶ እንደደረሰ ተገልጿል።

ኢንተርፕራይዙ ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመኾን በሚያደርገው ጉዞ የገቢ ምንጩን ለማሳደግ እየሠራ ነው ተብሏል።

በምረቃው ላይ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት፣ መሪዎች እና የከተማ አሥተዳደሩ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ ኾን ተብሎ በር ተዘግቶባታል።
Next articleየፎገራ ዳልጋ ከብቶችን ዝርያ ለማሳደግ ምን እየተሠራ ነው ?