
ደሴ፡ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሠንደቅ ዓላማ ሥርዓት ዘወትር ጠዋት እና ማታ በሚከበርበት ደሴ ከተማ ዓደባባይ ተከብሯል። የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ማክበር በክብር ስለ ሰንደቁ የወደቁትን ለማሰብ እና ለትውልድም አብሮነትን ማሳያ እንደሚኾን በበዓሉ ላይ የታደሙ የከተማው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ሠንደቅ ዓላማው በየቀኑ በከተማው አደባባይ ጠዋት እና ማታ መውጣቱ እና መውረዱ ልዩ ስሜት አለው ያሉት የከተማው ነዋሪዎች ትጋት እና ብርታትም ያጎናጽፋል ነው ያሉት።
የሕዝቦች የጋራ መለያ ከኾኑ እሴቶች አንዱ ሠንደቅ ዓላማ ነው ያሉት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ የደሴ ከተማ ሕዝብ ሠንደቅ ዓላማውን በማውጣት እና በማውረድ የሚገባውን ክብር እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የዚህ ዓመት የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር ለሰላም መስፈን እና ወቅቱ የሚጠይቀውን የልማት አርበኝነትን በመላበስ ሊኾን እንደሚገባም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ አበሻ አንለይ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!