
ከሚሴ፡ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 18ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን ”ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ መልዕክት በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አፈጉባኤ ፋጡማ ሞላ ሠንደቅ ዓላማችን የኅብረ ብሔራዊነታችን መገለጫ አርማችን ነው ብለዋል።
ሁሉም ሰው በተሰማራበት ሥራ ውጤት በማስመዝገብ ሀገሩን ሊጠብቅ ይገባል ነው ያሉት።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አሥተዳዳሪ ተወካይ መሐመድ ሲራጅ የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር የተከበረችና የታፈረች ሀገርን ለልጆቻችን ለማውረስ በትብብር መቆም ይገባናል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!