የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።

2
ደባርቅ: ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጸጥታ ችግር የሴቶች ጥቃት እንዲባባስ እያደረገ መኾኑን የሰሜን ጎንደር ዞን ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስተውቋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ኀላፊ ባንችዓምላክ መልካሙ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ምክንያት የሴቶች ተጋላጭነት መጨመሩን ተናግረዋል።
ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ ሕዝባዊ የንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ሢሠሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት የደረሰባቸውን ተጎጅዎች በተለያዩ ጉዳዮች የመደገፍ እና የመንከባከብ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የሴቶች እና ሕጻናት ክፍል ኀላፊ ኢንስፔክተር የኔአገኝ ጥጋቤ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ተፈጽመው ሲገኙም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የጸጥታ ችግሩ ፈታኝ መኾኑን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ጉዳዩን እስከፍጻሜው የመከታተል እና ወንጀለኞችን ለሕግ የማቅረብ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የደባርቅ አጠቃላይ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የሴቶችን ተወዳዳሪነት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚጎዳ ነው ብለዋል።
ሴቶች በሚደርስባቸው ጾታዊ ጥቃት እና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት ሕልማቸውን እውን ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት እየተገታ እንደኾነ ነው የገለጹት።
“የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም” ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየተሠሩ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ናቸው።
Next article18ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን በደብረ ታቦር ከተማ ተከብሯል።