
ባሕር ዳር: ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ሠንደቅ ዓላማው ታሪካችንን የምናወሳበት፤ የዛሬ ተግባራችን የምናጸናበት እና ነጋችንን የምንገነባበት ነው” በሚል መሪ መልዕክት 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በደብረ ማርቆስ ከተማ ተከብሯል።
በበዓሉ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳድር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ መርከብ የሻነው፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳደሪ ዋለ አባተን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የጸጥታ አካላት እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!