
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቢሾፍቱ ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የሥራ ኀላፊዎቹ በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የተሠሩ የሕዝብ መናፈሻ ቦታዎችን፣ የመንገድ ሥራዎችን እና የሞሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ዘጋቢ:- ዳግማዊ ተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!