
ደብረማርቆስ፡ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ 18ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ መልዕክት በወረዳው ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት ተከብሯል፡፡
የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ዋና አፈ ጉባኤ ማናየሽ ዳኜ “ጀግኖች አባቶች እና አያቶች ሀገርን ለመዳፈር የመጡ ወራሪዎችን የሕይወት መስዋትነት ከፍለው በመመከት ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት የኾነውን ሠንደቅ ዓላማ አስረክበውናል” ብለዋል፡፡
የሠንደቅ ዓላማን ክብር እና ከፍታ ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የሀገር ሉዓላዊነትን፣ አንድነትን እና ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማጽናት የሀገርን የዕድገት ከፍታ ማስቀጠል ከአሁኑ ትውልድ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡
የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ማማሩ አይንአበባ ለኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ሲሉ ብዙዎች መስዋዕት ከፍለውበታል፤ ብዙዎችም በኩራት በዓለም አደባባይ ሳይቀር በክብር አውለብልበውታል ብለዋል፡፡
ሠንደቅ ዓላማ የማንነት መገለጫ በመኾኑ ተገቢውን ክብር መስጠት ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!