ጀግኖች መስዋዕትነት የከፈሉለት የመሠባሠቢያ ሠንደቅ ዓላማ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተገቢው ክብር ሊሰጠው ይገባል።

16

እንጅባራ፡ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 18ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር እንጅባራ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

 

በዓሉ “ሠንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ መልዕክት ነው የተከበረው።

 

የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሙሉዓዳም እጅጉ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ተደርጋ ስትወሳ ሊቀራመቷት የፈለጉ ቅኝ ገዥዎች ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም።፤ ይልቅስ ለሠንደቅ ዓላማቸው ደማቸውን ያፈሰሱ እና አጥንታቸውን የከሰከሱ ጀግኖች በመኖራቸው ነው ብለዋል።

 

ይህ ጀግኖች መስዋዕትነት የከፈሉለት የመሠባሠቢያ ዓርማ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተገቢው ክብር ሊሰጠው እንደሚገባም ገልጸዋል።

 

ኢትዮጵያ እየተንደረደረችበት ወዳለው ከፍታ እንድትደርስ ሁሉም ዜጎች ለሀገራቸው ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም መከበር በጋራ መቆም እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሠንደቅ ዓላማችን የአንድነታችን ማጽኛ የጋራ አርማችን ነው።
Next articleኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጽናት የኢትዮጵያን የዕድገት ከፍታ ማስቀጠል ካሁኑ ትውልድ ይጠበቃል፡፡