የማኅበረሰቡን አንገብጋቢ ችግሮች እየፈታን ነው። 

3

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 03/2018ዓ.ም (አሚኮ) የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች አፈጻጸም እየገመገመ ነው።

 

የከተማ፣ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ መሪዎች በተገኙበት ነው ያለፉ የ90 ቀናትን ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ያለው።

 

የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፖርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ጊዜው ታከለ አርቆ ማሰብ እና አልቆ መሥራት ከሥራ መሪው እንደሚጠበቅ ጠቅሰዋል።

 

በከተማዋ የሥራ መሪዎች ያቀዱትን የመተግበር እና ውጤት የማምጣት መሻሻሎች መኖራቸውን ተናግረዋል። “የማኅበረሰቡን አንገብጋቢ ችግሮች እየፈታን ነው” ብለዋል።

 

የሚታረሙ የአፈጻጸም ጉድለቶች አሁንም እንዳሉ አንስተዋል። በቀጣይ 90 ቀናት ይህንን በማረም የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በሚያስችል አግባብ ያለው አመራር በመስጠት፣ ክትትል እና ድጋፍ በማጠናከር የተሻለ ሥራ የሚሠራበት መኾኑን ጠቁመዋል።

 

ለዚህም ዕቅዶችን ከከተማዋ ሕዝብ ጥቅም ጋር አስተሳስሮ ለመፈጸም ቁርጠኛ መኾን ይጠይቃል ብለዋል።

 

ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት የሠንደቅ ዓላማ ቀንን እያከበረ ነው። 
Next articleሠንደቅ ዓላማችን የአንድነታችን ማጽኛ የጋራ አርማችን ነው።