
ደሴ: ጥቅምት 01/02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሰሜን ምዕራብ እና ሰሜን ምሥራቅ ውጭ ግንኙነት ኀላፊ ጥላሁን ብርሃኑ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትምህርት እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር 56 ሚሊዮን ብር በበሽ ጥቅል ለእድለኞች ክፍት አድርጓል ብለዋል፡፡
ለ32 ሰዎች የአንድ ሚሊየን፣ ለ25 ሰዎች ደግሞ የመቶ ሺህ ብር እጣዎች በበሽ ጥቅል መዘጋጀታቸውን አንስተዋል። ሌሎች አነስተኛ እጣዎችንም በማዘጋጀት በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
እጣው በየሳምንቱ እና በየዕለቱ የሚወጣ ነው፤ ለባለእድለኞች ባሉበት ቦታ ያሸነፉትን ይረከባሉ ነው ያሉት፡፡
ከእነዚህ እድለኞች መካከል የደሴ ከተማ ነዋሪው አብዱ ሙሐመድ የአንድ ሚሊዮን ብር አሸናፊ ኾኗል፡፡
ሌሎች ሰዎች የእድሉ ተጠቃሚ እንዲኾኑ የመከረው ወጣት አብዱ በደረሰው ገንዘብ በተሰማራበት ልብስ ስፌት ሰፋ አድርጎ ለመሥራት ማቀዱን ተናግሯል፡፡
ዘጋቢ:- ባለ ዓለምየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!