ኮምቦልቻን በኢንደስትሪ ተመራጭ ለማድረግ ይሠራል።

3

ደሴ: ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።

በጉባኤው ከተማዋ በሎጅስቲክ እና በኢንዱስትሪ ተመራጭ እንዲትኾን የሚያስችላትን አሠራሮች እና ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ የተሠሩ ሥራዎች አበረታች መኾናቸውን የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።

በ2018 በጀት ዓመት የድጅታላይዜሽን፣ የሥራ እድል ፈጠራ እና የኢንቨስትመንት ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድ አሚን የሱፍ በከተማዋ የክልሉን የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ መሠረት ያደረገ ዕቅድ መታቀዱን ገልጸዋል።

የኮምቦልቻ ከተማን በሎጂስቲክ እና በኢንደስትሪ ተመራጭ ለማድረግ ከተማ አሥተዳደሩ በትኩረት እንደሚሠራ የገለጹት ከንቲባው የምክር ቤት አባላት ተገቢውን የክትትል እና የቁጥጥር ተግባራቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:- አበሻ አንለይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማኅበረሰቡን ጤና ማሻሻል ላይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።
Next articleጥራቱን የጠበቀ ምርት ለገበያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው።