
አዲስ አበባ: መስከረም 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ረቂቅ ፖሊሲ የመጨረሻ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ ሀገሪቱ ተቀብላ ለፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ሕጎች ተግባራዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል የመጀመሪያ እና ወጥ ፖሊሲ ለማዘጋጀት የሚያስችል ነው።
አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የመጨረሻ ግብዓቶችን ለማካተት የተዘጋጀ መኾኑን የኢፌዴሪ ሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሩያ አሊ ገልጸዋል።
ረቂቅ ፖሊሲው ከዚህ በፊት ለስምት ጊዜያት ውይይቶች ተካሂደውበታል ነው ያሉት። በተካሄዱ ውይይቶችም የአካል ጉዳተኞችን የእኩል ዕድል ተጠቃሚነትን እና ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ የፖሊሲ ግብዓቶች ተገኝተዋል።
በዛሬው ውይይትም ለሁሉም ምቹ የኾነች አካታች ኢትዮጵያን ለማየት ወጥ አሠራርን መዘርጋት የሚያስችል የፖሊሲ ግብዓቶችን ለመሠብሠብ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ ብቻ ሳይኾኑ ጠቃሚ እንዲኾኑ ለማስቻል ፖሊሲውን በፍጥነት በማጽደቅ ወደ ትግበራ ሲገባ ሁሉም ኀላፊነቱን እንዲወጣም ሚኒስትር ዴኤታ ሁሩያ አሊ ጥሪ አቅርበዋል።
በውይይት መድረኩ በረቂቅ ፖሊሲዉ ዙሪያ መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደም ነው።
ዘጋቢ፡- ኢብራሂም ሙሃመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!