የልማት እቅድ እውን እንዲኾን ሰላምን ማጽናት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ።

4
ደብረ ብርሃን: መስከረም 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ “ዘላቂ ሰላም ግባችን፣ አንድነት መንገዳችን ነው” በሚል መሪ መልዕክት የሕዝብ ንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።
የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በከተማው ሰላም እንዲሰፍን ሕዝብ እና የጸጥታ አካላት የነበራቸው ድርሻ ከፍተኛ እንደነበር ተናግረዋል። ይህንን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል።
በአማራ ክልል መንግሥት የተዘጋጀውን የ25 ዓመታት አሻጋሪ እና ዘላቂ የልማት እቅድ እውን እንዲኾን ሰላምን ማጽናት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል አቶ በድሉ።
ሰላምን ዘላቂ ለማድረግም የከተማዋ ሕዝብ በተለመደው አግባብ ለጸጥታ መዋቅሩ አጋዥ እንዲኾን ጥሪም አቅርበዋል።
በመድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደጀኔ ልመንህ እና ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት የፍርድ ቤቶች ሚና በሚል ርዕስ ለአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ስልጠና ተሰጠ።
Next article‎የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባትን በባሕር ዳር ከተማ መስጠት ተጀምሯል።