“የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

3

ባሕርዳር: መስከረም 29/2018ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በናይሮቢ ኬንያ እየተካሄደ በሚገኘው የኮሜሳ (COMESA) የመሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል እንዳቀረበልን አፅንኦት ሰጥቼ አንስቻለሁ ብለዋል።

እንደ አኅጉር የየሀገሮቻችንን ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጠናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክሂሎቱ እና መሠረቱ አለን ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ዲጂታል ክሂሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል። የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያን የማዳከም ዓላማ ያለው ሁሉ መሠባሠቢያው ግብጽ ነው”
Next articleበዘመቻ የሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት ውጤታማ እንዲኾን ሁሉም መረባረብ አለበት።