የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

2

ባሕር ዳር: መስከረም 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከመስከረም 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአማራ ክልል የዳኞች ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው ጨምሮ ሌሎች የክልሉ እና የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዛሬ በሚኖረው የመጨረሻ ቀን ውሎ መንግሥት ተከራካሪ የሚኾንባቸው የፍርድ ቤት ጉዳዮችን አያያዝ የተመለከተ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል።

የክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 የትኩረት አቅጣጫዎችም በጉባኤው ላይ ይቀርባሉ።

ፍርድ ቤቶች ከክረምት የእረፍት ጊዜ በኋላ ከጥቅምት መግቢያ ጀምሮ ወደ ችሎት መመለሳቸውን አስመልክቶም ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሥራ መመሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleነጋዴ ሴቶች ተወዳዳሪ እንዲኾኑ እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር አስታወቀ።
Next articleየውስጥ ኦዲተሮች ሙስናን ለመከላከል ከፍተኛ ድርሻ አላቸው።