የሆጤ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።

12
ደሴ፡ መስከረም 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ አሥተዳደር የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።
ማስፋፊያው በሰሜኑ ጦርነት መልሶ ማቋቋም እና ግንባታ መርሐ ግብር የተከናወነ ነው። የማስፋፊያ ግንባታው 12 መማሪያ ክፍሎች አሉት።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሰተባባሪ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፋተኛ የሥራ ኅላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን አምባቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአረጋውያን በምንም ነገር የማይተመኑ የሀገር ባለውለታዎች በመኾናቸው እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል።
Next articleለአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ዳኞች መሠረታዊ የኮሙዩኒኬሽን ስልጠና ተሰጠ።