አረጋውያን በምንም ነገር የማይተመኑ የሀገር ባለውለታዎች በመኾናቸው እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል።

7
ባሕር ዳር: መስከረም 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን ለአረጋውያን ደኅንነት እና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኀላፊነታችን እንወጣ በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ የማጠቃለያ ፕሮግራም እያካሄደ ነው።
በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ መልዕክታቸው አረጋውያን ሀገርን በነፃነት ያቆዩ የዕውቀት እና የጥበብ ባለቤት፣ የሀገር ባለውለታ ናቸው ብለዋል።
አረጋውያን በምንም ነገር የማይተመኑ የሀገራችን ባለውለታዎች በመኾናቸው ተንከባካቢ የሚያስፈልጋቸው፣ ድጋፍን የሚሹ ስለኾኑ ሁሉም በትኩረት ከእነርሱ ጎን ሊቆም ይገባል ብለዋል።
ሁሉም የኅበረተሰብ ክፍል አቅሙ በሚፈቅደው በቀሪ ዘመናቸው ከጎናቸው በመቆም ካበረከቱት ሀገራዊ አስተዋፅኦ አንጻር እውቅና በመስጠት ቀሪ ዘመናቸው የተሻለ እንዲኾን መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት እና ድርጅቶች የደገፏቸው ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ሰመሀል ፍስሀ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለማዕድን ልማት ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሠራ ነው።
Next articleየሆጤ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።