የክልሉ መንግሥት ለአምራች ኢንዱስትሪው የተለየ ትኩረት ሰጥቶታል።

10
ባሕር ዳር: መስከረም 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድን ከባንኮች፣ ከመሠረተ ልማት አቅራቢዎች፣ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከየባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ክልሉ ሰፊ የሚለማ መሬት እና ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች ያሉት ክልል መኾኑን ጠቅሰው ለቱረዝም የተመቼ መኾኑን አንስተዋል።
ባለፈው ዓመትም የክልሉ መንግሥትም ይህንን የተፈጥሮ ጸጋ ለማልማት የኢንቨስትመንት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ሥራ መሠራቱንም ጠቅሰዋል። በዚህም አበረታች ለውጥ ተመዝግበዋል ብለዋል።
በቁጥርም፣ በዓይነትም፣ በምርትም እያደገ ያለ ኢንቨስትመንት መኖሩንም ጠቅሰዋል።
ንቅናቄው ሲጀመር 44 ነጥብ 6 በመቶ የነበረው የማምረት አቅም በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ 59 ነጥብ 2 በመቶ መድረሱን አቶ እንድሪስ አንስተዋል።
ለስኬቱም የባለድርሻ አካላትን ሚና ጠቅሰዋል። የኀይል አቅርቦት ተቋማት ለአምራች ኢንዱስትሪው እጥረት እንዳይኖር ሲያግዙ መቆየታቸውንም አንስተዋል።
የክልሉ መንግሥት በዘርፉ የ25 ዓመት አሻጋሪ እቅድ አዘጋጅቶ በየደረጃው ማስተዋወቁን የገለጹት አቶ እንድሪስ ይህ ውይይትም የዚያው አካል መኾኑን ተናግረዋል። የዘርፉ የ10 ዓመት እቅድ ላይ ለመወያየት መኾኑን አንስተዋል።
የክልሉ መንግሥት ለአምራች ኢንዱስትሪው የተለየ ትኩረት ሰጥቶታል። ተቋሙም የራሱን እቅድ አዘጋጅቷል።
ይህንን ስትራቴጅክ እቅድ ለማሳካት የባለድርሻ አካላትን ግልጽነት በመፍጠር በትብብር ለመሥራት እና ተልዕኮ ለመቀባበል መኾኑን ነው ኀላፊው የገለጹት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየዓሣ ሃብትን ለማሳደግ ምን እየተሠራ ነው?
Next articleበበጀት ዓመቱ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ወጋገን ባንክ አስታወቀ።