ወጣቶችን በተለያዩ መስኮች ለማብቃት እና ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው።

5
አዲስ አበባ: መስከረም 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “በለውጡ የተለወጠ ወጣት” በሚል መሪ መልዕክት 8ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ፌስቲቫል የማጠቃለያ መርሐ ግብር በታላቁ ብሔራዊ ቴአትር መካሄድ ጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኅላፊ በላይ ደጀን ወጣቶችን በተለያዩ መስኮች ለማብቃት እና ተጠቃሚ ለማድረግ ከተማ አሥተዳደሩ በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በሚገኙ በ114 የወጣቶች የስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ከሚሰጡ 18 ዓይነት አገልግሎቶች መካከል የወጣቶች የኪነ ጥበብ እና ሥነ ጥበብ ተሰጥኦ ማሳደጊያ አንዱ ነው ብለዋል።
በዚህም በ518 ቡድኖች መካከል ሲደረግ የቆየው የኪነ ጥበብ ውድድር 152 ወጣቶች በዘመናዊ እና ባሕላዊ ውዝዋዜ ውድድር ሲሳተፉ ቆይተዋል።
በ8ኛው የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች የማጠቃለያ መርሐ ግብርም የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ለደረሱ አሸናፊዎች ሽልማት መዘጋጀቱ ታውቋል።
ዘጋቢ:- ድልነሳ መንግሥቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ128 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት ማዳን ተችሏል።
Next articleየዓሣ ሃብትን ለማሳደግ ምን እየተሠራ ነው?