
ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት “ከጂኦ እስትራቴጅያዊ ኩስመና ወደ ታደስ ቁመና” በሚል መሪ መልዕክት ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ኀላፊ ማዕዛ በዛብህ “እኛ ኢትዮጵያዊያን ባለብዙ ታሪክ እና የዘርፈ ብዙ እሴቶች ባለቤት ነን” ብለዋል።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለመቀየር ኢትዮጵያውያን እጅ እና ጓንት ኾነው በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። ወደ ተጀመረው የስኬት መንገድ ለመጓዝ የሁሉንም ርብርብ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።
ለውጡ የሚጀምረው ከራስ ነው ያሉት ኀላፊዋ ሕዝቡን በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ መኾኑን ገልጸዋል።
ማንኛውም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደስተኛ እና በአገልግሎቱ እንዲረካ በማድረግ በጋራ ወደ ከፍታ ማማ መጎዝ ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ሰመሀል ፍስሀ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!