
ባሕር ዳር: መስከረም 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የደም ልገሳ አድርገዋል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተህልቁ፣ የሰነደ መዋለ ንዋይ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ.ር) እና ከሁሉቱም ተቋማት ከፍተኛ መሪዎች እንዲሁም ባለሙያዎች ጋር በመኾን የደም ልገሳ መርሐ ግብሩን አስጀምረዋል።
ደም ልገሳ በደም እጥረት የሚከሰትን ህልፈት ሕይዎት የሚታደግ በመኾኑ ዜጎች እንደ ባሕል ሊይዙት የሚገባ ሰብዓዊ ተግባር እንደኾነ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎችም ደም እንዲለግሱ ማበረታታቸውንም ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!