ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ተልዕኮን በአግባቡ መወጣት ይገባል።

4
ደብረ ማርቆስ: መስከረም 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃ ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሕግ ማስከበር ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ በደጀን ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ በሕግ ማስከበር ተግባራት ላይ በተጨባጭ የተገኙ ውጤቶችን እና ውስንነቶችን በመፈተሸ ለተሻለ አፈጻጸም መትጋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በየአካባቢው ያለውን ተጨባጭ የሕግ ማስከበር አፈጻጸሞችን በአግባቡ በመገምገም እና የጋራ መግባባት በመፍጠር ተልዕኮን በአግባቡ መወጣት እና ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ውይይቱ የተጀመሩ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ኅብረተሰቡን ከገጠመው የሰላም ዕጦት ለማውጣት የሚያስችሉ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት እንደኾነም አስገንዝበዋል፡፡
አንድነትን በመላበስ “ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ተልዕኮን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባም” አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የመከላከያ ሠራዊት መሪዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአካባቢን በማጽዳት ወባን በቀላሉ መከላከል ይቻላል።
Next articleየውኃ ጉድፍ በሽታ ምንድን ነው?