ከደብረ ብርሃን-ደነባ-ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር-ደነባ የአስፓልት መንገድ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተከናወነ ነው፡፡

449

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 06/2012 ዓ.ም (አብመድ) ከ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የደብረ ብርሃን-ደነባ-ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር-ደነባ የአስፓልት መንገድ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተከናወነ ነው፡፡

ግንባታውን ያስጀመሩት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና ሌሎች የፌዴራልና የአማራ ክልል መንግሥት የሥራ ኃፊዎች ናቸው፡፡

ከደብረብርሃን-ደነባ-ለሚ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ 108 ኪሎ ሜትር እንደሚረዝም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ የመንገድ ግንባታው በአራት ዓመታት ውስጥ እንዲጠናቀቅ የጊዜ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡ ለዚህም ከ3 ቢሊዮን 613 ሚሊዮን 767 ሺህ ብር በላይ በጀት ተመድቦለታል፡፡

ወጪው በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ነው፡፡ ግንባታን የሚያከናውነውም ሰንሻይን የግንባታ ተቋራጭ ነው፡፡

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ ከግንባታ ማስጀመሩ ቀደም ብሎ በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ፎቶ፡- በይርጉ ፋንታ

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleከ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ሚኒስቴሩ ገለጸ፡፡
Next articleየአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና በመጭው ጥር ይጀምራል፡፡