በዓለም አቀፍ ደረጃ በምጣኔ ሃብት ተስተካካይ ሀገር ለመፍጠር ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ካፒታልን ከቴክኖሎጂ ጋር ማቀናጀት ያስፈልጋል።

8

ባሕር ዳር: መስከረም 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች ጉባኤ እንደቀጠለ ነው።

በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር የኢኮኖሚ ቴክኒካል አማካሪ እና የልማት እቅዱ ተቀዳሚ ፕላነር ሰኢድ ኑሩ (ዶ.ር) የክልሉን የ25 ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ አቅርበዋል።

ዶክተር ሰኢድ በምጣኔ ሃብት እድገት ንድፈ ሀሳብ መሠረት ቁሳዊ ካፒታል፣ ሰብዓዊ ካፒታል እና ቴክኖሎጂ የሀገራትን በነፍስ ወከፍ ገቢ መበላለጥ የሚወስኑ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል። የኢኮኖሚ እድገት ምንጭ ተደርገውም ይወሰዳሉ።

ከዚህም ባለፈ ቁጠባ፣ መዋዕለ ንዋይ እና ትምህርትን ከድህነት መውጫ መንገዶች መኾናቸውን ነው የገለጹት። በርካታ በድህነት ውስጥ የሚገኙ ሀገራት ለእነዚህ ጉዳዮች ትኩረት ቢሰጡም ከድህነት መውጣት የቻሉት ግን ጥቂቶች መኾናቸውን አንስተዋል።

እንደ አማራ ክልል ብሎም እንደ ሀገር ካለፉት መንግሥታት ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን የልማት እቅድ ሰነዶች መካተታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይ ፈጣን እና አሻጋሪ የኢኮኖሚ እድገት እንዲረጋገጥ እንደ ማኅበረሰብ
ቁጠባን ማበረታታት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ከሌሎች ምንጮች የተገኘን የልማት ፋይናንስም ለመዋቅራዊ ሽግግር መሳካት ቁልፍ ሚና ባላቸው ምጣኔ ሃብታዊ ዘርፎች ላይ ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህንም በሥልጠና እና በምርምር ማጠናከር ከተቻለ በምጣኔ ሃብት እድገት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተስተካካይ ሀገር መኾን እንደሚቻል ነው ያነሱት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየድህነት እና የኋላቀርነት ማምከኛ ብልሃቱ የተማረ ዜጋ መፍጠር ብቻ ነው።
Next articleፕሮግራሙ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ የመንግሥትን ልዩ ትኩረት ይፈልጋል።