“ዛሬ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚያኮራ ታሪካዊ ሁነት ተፈፅሟል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

47

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሠረት አስቀምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚያኮራ ታሪካዊ ሁነት ተፈፅሟል ብለዋል። የሁለት አሻጋሪ ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ የሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሠረት አስቀምጠናል ነው ያሉት።

የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለው። በሌላ በኩልም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል ብለዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢንደስትሪ እድገትን ከማሳየት በላይ ናቸው። እድሎቻችንን የመጠቀም፣ ትብብሮችን የማጠናከር እና ሰላምን የማጽናት የጋራ ኃላፊነታችንን የሚያሳዩ ናቸው ነው ያሉት።

በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በኅብረት እና በአንድነት ለእድገት መሰባሰባችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ። ይኽን ስናደርግ እውነተኛውን የኢትዮጵያዊ ማንነት መንፈስ በሚያከብር መንገድ በዓለም መድረክ የኢትዮጵያን ስፍራ ከፍ እናደርጋለን ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዳግም ትምህርቴን እንድማር ዕድሉ ስለተሰጠኝ እንደገና የመወለድን ያህል ቆጥሬዋለሁ” ትምህርት አቋርጦ የነበረ ተማሪ
Next articleመናኻሪያዎች ዲጂታል የትኬት አገልግሎትን መጠቀማቸው የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ያደርገዋል።