
ደብረማርቆስ፡ መስከረም 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ዕቅዶች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።
በከተማው በመሠረተ ልማት ዘርፍ የተሠሩ ሥራዎች ክንውንን በመገምገም በተያዘው በጀት ዓመት ሊሠሩ የታቀዱ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይም ምክር ቤቱ ውይይት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።
በጉባኤው የከተማው አሻጋሪ የዕድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድም በከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
የከተማ አሥተዳደሩ የ2018 በጀት ድልድልም ለምክር ቤቱ ቀርቦ እንደሚጸድቅ ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!