ከ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ሚኒስቴሩ ገለጸ፡፡

195
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 05/2012 ዓ.ም (አብመድ) ከ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በሁለት ቀናት ብቻ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው እንደገለጹት ትናንት ሰኔ 4/2012 ዓ.ም ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሊገባ ሲል በአንድ ተሽከርካሪ ላይ በተደረግ ጥብቅ ክትትል እና ፍተሻ ግምቱ 368 ሺህ ብር የሚያወጣ የኮንትሮባንድ ጎማ ተይዟል፡፡
 
በዕለቱ በተደረገ ሌላ ፍተሸ ደግሞ በመኪና ውስጥ በተሠራ መደበቂያ 1 ሚሊዮን 947 ሺህ 985 የኢትዮጵያ ብር ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሲሞከር ተይዟል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
 
እንደ አቶ ላቀ ገለጻ ሰኔ በ03/2012 ዓ.ም ደግሞ 1 ሚሊዮን 541 ሺህ 660 ብር የሚያወጣ 770 ነጥብ 83 ኪሎ ግራም ወርቅ ተይዟል።
 
በሁለት ቀናት ብቻ በተደረገ ፍተሻ በሦስቱ ዓይነት ዕቃዎች ብቻ 3 ሚሊዮን 857 ሺህ 645 ብር የሚያወጣ ሀብት በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
 
ለሥራው አስተዋጽዖ ላደረጉ የጉምሩክ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞች እና የፌደራል ፖሊስ አባላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ተጨማሪ መረጃዎችን በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡
Previous articleወረርሽኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናትን ለጉልበት ብዝበዛ ሊዳርግ እንደሚችል ተመድ አሳሰበ፡፡
Next articleከደብረ ብርሃን-ደነባ-ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር-ደነባ የአስፓልት መንገድ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተከናወነ ነው፡፡