የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ በጀትን አጸደቀ።

4
እንጅባራ: መስከረም 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም በጀትን ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ አድርጎ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን 4ኛ ዙር 33ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ማሥፈጸሚያ በጀትን በማጽደቅ አጠናቅቋል። በጀቱም 7 ቢሊዮን 713 ሚሊዮን 81 ሺህ 526 ብር ኾኖ ጸድቋል።
የተመደበው በጀት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ አለውም ተብሏል። ከተመደበው በጀት 25 በመቶ የሚኾነው ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የካፒታል በጀት የተመደበ እንደኾነም በዕለቱ ተነስቷል።
የበጀት ዕቅዱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ገንዘብ መምሪያ ኀላፊ መለሠ አዳል ተቋማት እቅዶቻቸውን ከተመደበላቸው በጀት ጋር አጣጥመው እንዲፈጽሙ አሳስበዋል።
በተዋረድ ያሉ ምክር ቤቶች የተመደበው በጀት ለታለመለት አላማ ስለመዋሉ የቁጥጥር እና የክትትል ሥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ኀላፊው አስገንዝበዋል።
ከተመደበው በጀት ውስጥ ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚኾነው በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከሚሰበሰበው ገቢ የሚሸፈን ነው ያሉት ኀላፊው በገቢ አሠባሠቡ ላይ በትኩረት መሠራት እንደሚገባም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ሳሙኤል አማረ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleጤና ሚኒስቴር ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚቆየውን ሁለተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና ደህንነት ትግበራ ይፋ አደረገ።
Next articleየሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የፍትሕ ተቋማት የቀጣይ ትኩረት ነው።