
ባሕር ዳር: መስከረም 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ዓመታዊ የንግስ በዓል በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መምህር አባ ለይኩን የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መምህር አባ ብስራተ ገብርኤል የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ቤተክርስቲያን ዋና አሥተዳዳሪ፣ የገዳማት እና የአድባራት አሥተዳዳሪዎች እና ከተለዩዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሰባሰቡ በርካታ ምእመናን በዓሉን እያከበሩ ነው።
መረጃው የደቡብ ወሎ ኮሙኒኬሽን ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለ