የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

5
ሰቆጣ፡ መስከረም 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት 31ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱም የ30ኛ መደበኛ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣ የ2017 በጀት ዓመት የአሥፈጻሚውን ዕቅድ ክንውን ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ፣ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የአሥፈጻሚውን ፊዚካል እና የፋይናንስ ዕቅድ መርምሮ ማጽደቅ እና የብሔረሰብ ምክር ቤቱን የ2018 ዓ.ም በጀት መርምሮ ማጽደቅ በሚሉ አጀንዳዎች ዙርያ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።ምክር ቤቱ የሚያካሂደው ጉባኤ ከመስከረም 21/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 22/2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይም ለማወቅ ተችሏል።
ዘጋቢ፦ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ደጋጎቹ የሚናፍቁሽ፤ ብርሃን ያረፈብሽ”
Next articleአረጋውያንን መርዳት የዜጎች ግብረ ገባዊ ግዴታ መኾን አለበት።