በ2017 በጀት ዓመት አበይት ተግባራትን በመፈጸም ስኬታማ እንደነበር ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

7
ባሕርዳር፡ መስከረም 20/2018ዓ.ም (አሚኮ) ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ እያካሄደ ነው።
የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መብት አድማስ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ዓበይት ተግባራትን በመፈጸም ስኬታማ ጊዜን ያሳለፍንበት ዓመት ነበር ብለዋል። ዓመቱ የተቋም ስያሜ እና የአደረጃጀት ለውጥ ያደረገበት፣ የኮርፖሬሽኑን መሪዎች እና ሠራተኞች በአዲስ ምደባ ያደረገበት ነበር ነው ያሉት። ኮርፖሬሽኑ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ በማከናወን ከ544 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ያስመዘገበበት እንደነበር ነው የገለጹት።
የተቋሙን ሥራ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እንዲቻል ቴክኖለጅን ያበለጸግንበት፣ የባሕር ዳር ከተማን የኮሪደር ልማት ሥራ በፍጥነት እና በጥራት በመገንባት የከተማውን ገጽታ ያሳመርንበት ተግባር ዋና ዋናዎቹ ውጤታማ ሥራዎች ነበሩ ነው ያሉት።
የክልሉ መንግሥትም ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ላከናወናቸው ውጤታማ ሥራዎች በቅርቡ ዕውቅና ሰጥቶታል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እንግዶቿን እየተቀበለች ነው፡፡
Next article“ትምህርት ካቋረጥኩ ብዙ ጊዜ ስለሆነኝ ብዙ ነገሩን ረስቸዋለሁ” ትምህርት አቋርጣ የቆየች ተማሪ