
እንጅባራ: መስከረም 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 33ኛ መደበኛ ጉባኤውን በእንጅባራ ከተማ እያካሄደ ነው።
የብሔረሰብ ምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ሙሉዓዳም እጅጉ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ውጤት የተመዘገባቸው በርካታ ሥራዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል። የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሰላም እና የልማት ሥራዎች እንዲሳለጡ የምክር ቤት አባላት ጉልህ ሚና ተጫውተዋልም ነው ያሉት።
የዴሞክራሲ ግንባታ እና የልማት ሥራዎችን በማስተሳሰር የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የምክር ቤት አባላት ከዚህ በላይ መትጋት እንደሚጠበቅባቸውም አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የ2017 በጀት ዓመት የአሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርት እንዲኹም የ2018 በጀት ዓመት እቅድ እና የማስፈፀሚያ በጀት መርምሮ ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!