የእንግሊዝ ምጣኔ ሀብት ከ20 በመቶ በላይ ቅናሽ ማሳየቱን ብሔራዊ የስታትስቲክስ ማዕከል ገለጸ፡፡

135

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 05/2012 ዓ.ም (አብመድ) በሚያዝያ በነበረ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት የእንግሊዝ ምጣኔ ሀብት በ20 ነጥብ 4 በመቶ መውረዱን ብሔራዊ የስታትስቲክስ ማዕከል አስታውቋል፡፡

የምጣኔ ሀብት ማሽቆልቆሉ እ.አ.አ ከ2008 እስከ 2009 ከነበረው በሦስት እጥፍ የከፋ መሆኑንም ማዕከሉ አመልክቷል፡፡

በሚያዝያ በየካቲት ከነበረው አንጻር እስከ 25 በመቶ ድረስ ማሽቆልቆል እንደነበረ ያመለከተው መረጃው በእንግሊዝ ታሪክ ተመዝግቦ የማያውቅ የምጣኔ ሀብት ድቀት እንደሆነም አሳይቷል፡፡ በምጣኔ ሀብት ቀውሱ ያልተመታ ዘርፍ ባይኖርም የመዝናኛ፣ የትምህርት፣ የጤና እና የመኪና አምራችና የግንባታ ኢንዱስትሪው ክፉኛ መጎዳቱን መረጃው አመላክቷል፡፡

ምጣኔ ሀብቱ መቼ በደንብ እንደሚያገግም እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ያስታወቀው ብሔራዊ የስታትስቲክስ ማዕከሉ ከሚያዝያው የከፋ የምጣኔ ሀብት ማሽቆልቆል እንደማይገጥም ግን ተስፋ አድርጓል፡፡ የእንቅስቃሴ ገደቦቹ እየላሉ መሆኑን የተመለከቱ የምጣኔ ሀብት ተንታኞችም ተመሳሳይ ተስፋ አላቸው፡፡

እንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ጨምሮ 291 ሺህ 409 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘውባታል፤ የ41 ሺህ 279 ሰዎች ሕይወት ደግሞ አልፏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
በአብርሃም በዕውቀት

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየተማሩትን ወደ ተግባር የቀየሩ ወጣቶች የገበያ ትስስር ችግር ገጥሟቸዋል፡፡
Next articleወረርሽኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናትን ለጉልበት ብዝበዛ ሊዳርግ እንደሚችል ተመድ አሳሰበ፡፡