ለሰላም እጦት ምክንያት የኾኑ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በመፍታት ዕቅዶችን ለማሳካት ይሠራል።

11

ፍኖተ ሰላም፡ መስከረም 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ”አርቆ ማየት አልቆ መሥራት” በሚል መሪ መልዕክት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

 

በመድረኩ ላይ የተገኙት የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ጊዜው ደግአረገ ምንም እንኳ የጸጥታ ችግሩ እንቅፋት ቢፈጥርም በከተማ አሥተዳደሩ በ2017 በጀት ዓመት ከሰላም ግንባታው ጎን ለጎን የልማት ሥራዎችን ማከናወን ተችሏል ብለዋል።

 

በተለይ በኮሪደር ልማት የተቋማትን የሥራ ከባቢ ምቹ ማድረግ እንደተቻለም ነው ያስገነዘቡት።

 

በ2018 በጀት ዓመት ያለፉት ዓመታትን በሚያካክስ መልኩ የተለያዩ የልማት ሥራዎች በትኩረት በመሥራት የአሻጋሪ ዕድገት እና የዘላቂ ልማትን ዕውን ለማድረግ እንደሚሠራም ምክትል ከንቲባ ጊዜው ደግአረገ ገልጸዋል።

 

የወንዝ ዳርቻ እና የከተማ ኮሪደር የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ከማኅበረሰቡ ጋር በመኾን በትኩረት ይሠራልም ነው ያሉት።

 

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የታዩ ስኬቶችን የበለጠ በማስፋት በቀጣይ የአሻጋሪ ዕድገት እና ዘላቂ ልማት በተሻለ ለመፈፀም መሥራት እንደሚገባም አንስተዋል።

 

የታቀዱ የልማት ሥራዎችን በስኬታማነት ለመፈፀም ኅብረተሰቡን አሳትፎ በቅንጅት መሥራት እንደሚጠይቅም ተናግረዋል።

 

የሰላም እጦት ምክንያት የኾኑ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሠሩም ገልጸዋል።

 

የታቀዱ የልማት ተግባራትን እውን ለማድረግ ገቢን በውጤታማነት መሠብሠብ እንደሚያስፈልግም ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

 

የገቢ አቅምን አሟጦ በመጠቀም እና በመሠብሠብ የአሻጋሪ ዕድገት እና ዘላቂ ልማት ዕቅዱን ዕውን ለማድረግ እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በችግር ውስጥም ኾነው ስኬታማ የኾኑ ተማሪዎች ምሥጋና ይገባቸዋል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) 
Next articleሕጻናትን ማስከተብ የሁሉም ኀላፊነት ሊኾን ይገባል።