የሕዝብን የመልማት ፍላጎት የሚያሳካ ዕቅድ በማቀድ ወደ ሥራ መግባት ወሳኝ ነው።

5
ደብረ ማርቆስ: መስከረም 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከአጠቃላይ የመምሪያ ኀላፊዎች እና ሠራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ በላይ የዞኑን የመልማት አቅም በጥናት በመለየት በሰው ሃብት ልማት፣ በቴክኖሎጂ እና በካፒታል በመታገዝ የታቀዱ ተግባራትን መፈጸም እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የምሥራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ዋለ አባተ ባለፈው የ2017 በጀት ዓመት የዞኑን የኢኮኖሚ ጸጋዎች በመለየት ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
በጸጥታ ችግርም ውስጥ ኾኖ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊ፣ በሕግ ማስከበር እና በመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ ተናግረዋል። የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድን መነሻ ያደረገ ተግባር በማቀድ ወደ ሥራ እንደሚገባም አንስተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ሀገሬን የሚጠቅም ሥራ ለመሥራት ተዘጋጅቻለው” ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ
Next article“የእናንተ ውጤትም ችግርን የማሸነፍ እሳቤ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)