
ደብረ ብርሃን: መስከረም 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የጀግኖች ማዕከል ግንባታን በደብረ ብርሃን ከተማ አስጀምሯል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ የፖሊስን ዋጋ እና ክብር የሚመጥን ማዕከል ነው የሚገነባው ብለዋል።ኮሚሽነሩ ለማኅበረሰቡ ሲል ዋጋ የከፈሉ የፖሊስ አባላት ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ እና እንዲቋቋሙ የሚያያችል ማዕከል የሚገነባ ስለመኾኑም አንስተዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የማዕከሉ ግንባታ እንዲፋጠን አስፈላጊውን መሠረተ ልማት በማሟላት ከተማ አሥተዳደሩ ኀላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።
ለከተማው ልማት እና ለሀገር እድገት የፖሊስ ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ይህንን ውለታቸውን በአግባቡ መክፈል ይገባልም ነው ያሉት።በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የክልል፣ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ለዓለም ለይኩን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!