“የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመሻገር የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ ነው” ባንቺዓምላክ ገብረ ማርያም

6
ባሕር ዳር: መስከረም 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ባንቺዓምላክ ገብረ ማርያም መንግሥት የአግልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መኾኑን ተናግረዋል።የመንግሥት አገልግሎት ዘገምተኛ መኾን፣ የግልጽነት ችግር ያለበት፣ ተጠያቂነት የሌለበት ኾኖ መቆየት የሕዝብ የመልካም አሥተዳደር ችግር ኾኖ ቆይቷል ነው ያሉት። ሕዝብን ሲያማርር መቆየቱንም አንስተዋል።
ችግሮችን ለመሻገር የተለያዩ ተግባራት እየተሠሩ መኾናቸውን ኀላፊዋ ተናግረዋል። የአገልግሎት ችግሮችን ለመፍታት እንደ ሀገር የሪፎርም ሥራዎች መሠራታቸውንም ነው ያነሱት። የአማራ ክልል መንግሥትም እንደ ሀገር የተጀመረውን ሪፎርም እየተገበረ መኾኑን ገልጸዋል። ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ የክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩን ተናግረዋል። በቀጣይም በደሴ እና በጎንደር ከተሞች መሶብ የአንድ አገልግሎትን ለማስጀመር እየተሠራ መኾኑን ነው የገለጹት።
ዛሬ የተመረቀው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በ45 ቀናት መጠናቀቁን ገልጸዋል። በቀጣይ የተጀመሩ ሥራዎችን በማስቀጠል ወደ ሪጂዮፖሊታንት ከተሞች ለማውረድ እንደሚሠራም ተናግረዋል። የክልሉ ሕዝብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩን በመረዳት የአግልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ጥሪ አቅርበዋል።በማዕከሉ የተመደቡ ሠራተኞች በቅንነት እንዲያገለግሉም አሳስበዋል። ሥራው ውጤታማ እንዲኾን ላደረጉ ሁሉ ምስጋናም አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየመስቀል በዓል በመስቀለኛው ቦታ ይቋጫል።
Next articleየጀግኖች ማዕከል ግንባታ በደብረ ብርሃን ከተማ ተጀመረ።