“የመስቀሉ መገኘት ለዓለም አንድነትን የሰጠ የመዳን ምልክት ነው” ብጹዕ አቡነ በርናባስ

4
ሰቆጣ: መስከረም 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመስቀል በዓል በሰቆጣ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በበዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያሥተላለፉት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ በርናባስ ለ300 ዓመታት ተቀብሮ የነበረው የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በንግስት እሌኒ ፈላጊነት ከተዳፈነበት መገኘቱን ተናግረዋል።
ንግስት እሌኒ ከተዳፈነበት ተራራ መስቀሉን ፈልጋ እንዳገኘችው ሁሉ ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ ተዳፍኖ ያለውን ሰላምና አንድነት፣ ፍቅርና መቻቻል ፈልገን ልናገኘው ይገባል ብለዋል። መስቀል የፍቅር ምልክት ለሚያምኑት የድኅነት ማኅተም ነው ያሉት ብጹዕ አቡነ በርናባስ በዓሉን በመከባበርና በመደጋገፍ ልናከብር ይገባል ነው ያሉት።
የመስቀሉ መገኘት ለዓለም አንድነት የሰጠ የመዳን ምልክት በመኾኑ ዛሬም የመስቀሉን በዓል ስናከብር ስለሀገር ሰላምና ፍቅር በመጸለይና በማሰብ ሊኾን እንደሚገባ ተናግረዋል።የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ፣ የተራቡትን በማብላት፣ የተጠሙትን በማጠጣት በዓሉን ማክበር ክርስቲያናዊ ትዕዛዝ ብቻ ሳይኾን ሰብዓዊነት መኾኑን ነው ለምዕመኑ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ: ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየመስቀል በዓል አድማቂው ”አብዚ”
Next article“በመስቀል ማዕበል ያልፋል፤ በመስቀል መከራ ይታለፋል”